You are currently viewing ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከሰላም የሕፃናት መንደርና ከሲዲሲ ጋር ተፈራረመ

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከሰላም የሕፃናት መንደርና ከሲዲሲ ጋር ተፈራረመ

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከሰላም የሕፃናት መንደርና ከሲዲሲ ጋር ተፈራረመ

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለውን ስምምነት ከሰላም የሕፃናት መንደር (Selam Children’s Village) እና ከኢትዮጵያን ንተር ፎር ዴቨሎፕመንት (ECD) ጋር የካቲት 10/2014 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በቪዥንፈንድ በኩል ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ (የኦፕሬሽን) አቶ ሀይሉ ለታ እና ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ (ሰፖርት ሰርቪስስ) አቶ ሰለሞን ወ/ጊዮርጊስ ሲሆኑ፤ ከኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ወ/ሮ ሀረገወይን አሸናፊ ኤክሲኩቲቭ ዳይሬክተርና ከሰላም የሕፃናት መንደር ደግሞ አቶ ሰለሞን ጫሊ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ በሶስቱ ተቋማት ጥምረት የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት “ዘ ፓርትነርስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን የስምምነቱ አላማ በንግድ ስራ ላይ ለሚሰማሩ ወጣት ሴቶችን እና ወንዶችን የፋይናንስ አገልግሎትን በማመቻቸት በገበያ ውስጥ የተሻለ ተወዳዳሪና ተሳታፊ የሚያደርጋቸው ብሎም ዘላቂ የንግድ ግንኙነት መፍጠር መሆኑ ተገጿል። የፕሮጀክቱ ትግበራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሲሆን ወጣቶቹ የተሻለ የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ በቁጠባና ብድር አገልግሎት ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አካታች የፋይናንስ አገልግሎቶች ባሉት 96 ቅርንጫፎች ሁሉ እየሰጠ ያለ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት በወጣቶች መካከል የረዥም ጊዜ ግንኙነት በመፍጠር ለወጣቶች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት መሰረት ለመጣል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ወጣቶች ሥራን የመናቅ ኋለ-ቀር አስተሳሰብ ተላቀው ባገኙት አጋጣሚ ተጠቅመው እራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን ለመለወጥ ተግተው መስራት እንዳለባቸው በዕለቱ ሶስቱም ተቋማት የተወያዩበት ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዚህ ፕሮጀክት ትግበራ ስኬት ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግእንዳለባቸው ተስማምተዋል፡፡ “ዘ ፓርትነርስ” ፕሮጀክት ትግበራ እስከ 2024 እ.ኤ.አ ድረስ የሚቆይ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply