You are currently viewing የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሠራተኞች የገናን በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሠራተኞች የገናን በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል

 

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሠራተኞች የገናን በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ዋና መ/ቤት ሠራተኞች የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በዋና መ/ቤት አደራሽ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡ በዕለቱ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳ ሲሆኑ ገና ለክርስትና እምነት ተከታይ ከመብልና መጠጥ ያለፈ ትርጉም አለው በእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡ እንደ ተቋም በግማሽ አመት እግዚአብሔር ረድቶን በብዙ ስኬት እየተጓዝን ሲሆን፤ ሁሉም ቅርንጫፎቻችን በኮርባንኪንግ ሲስተም ለማገናኘት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡ አክለውም በሰሜን ማስተባበሪያ ስር የሚገኙት ቅርንጫፎቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ለመለየትና መልሶ ሥራ ለማስጀመር የጥናት ቡድን ተዋቅሮ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ጉዳት የደረሰባቸው ቅርንጫፎቻችን መልሶ ወደ ሥራ የማስገባት ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

Leave a Reply