You are currently viewing የሀዋሳ ቅርንጫፍ ከ30ሚ ብር በላይ ለሴቶች ብድር መስጠቱን ገለጸ

የሀዋሳ ቅርንጫፍ ከ30ሚ ብር በላይ ለሴቶች ብድር መስጠቱን ገለጸ

የሀዋሳ ቅርንጫፍ ከ30ሚ ብር በላይ ለሴቶች ብድር መስጠቱን ገለጸ

ቪዥንፈንድ ማክሮፋይናንስ አ.ማ ሐዋሳ ቅርንጫፍ በ2014 ዓ.ም በ6 ወር ብቻ ለሴቶች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ስንታየው ባዩ ገልጸዋል፡፡ ቅርንጫፉ ሴቶችን በቁጠባና ብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ላለፉት በርካታ
አመታት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተሰራው ሥራ በሀዋሳ ከተማና በአካባቢ የገጠር ቀበሌዎች የሚኖሩ ሴቶች አመርቂ ውጤት ታይቷል፤ ሴቶች በኢኮኖሚ እራሳቸውን ከመቻል አልፈው ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር ለሀገር እድገት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ተገልጿል፡፡
የተቋሙ ፖሊሲ በዋናነት ሴቶችን የፋይናንስ አገልግሎቶችን ግንባር ቀደም ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን የገለጹት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጇ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ለተሰማሩትና የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት እቅዳቸውን እንዲያሳኩ በተዘጋጀው የብድር አይነቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅርንጫፉ አጽንኦት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ብድር አመላለስ ላይ ለሴቶች የተሰጠ ብድር ሙሉ በሙሉ ማስመለስ መቻሉ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል፡፡ ለስኬቱ መሰረት የሆነው በቅድመ ብድርና በድህረ ብድር የሚደረገው ቢዝነስ ክትትልና ድጋፍ መሆኑ ወ/ሮ ስንታየው ይናገራሉ፡፡
ሐዋሳ ቅርንጫፍ ቁጠባን ለማበረታታት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የኅብረተሰቡን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ በቁጠባ ረገድ በተቋሙ ውጤት መገኘቱ ተገልጿል፡፡ የቅርንጫፉ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነትና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ በደንበኞች ዘንድ ተቋሙን ተመራጭ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ያደርገዋል ብለዋል ወ/ሮ ስንታየው ባዩ የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ፡፡

Leave a Reply