You are currently viewing በተጠና መንገድ ብድር በመስጠት ላይ እንገኛለን

በተጠና መንገድ ብድር በመስጠት ላይ እንገኛለን

በተጠና መንገድ ብድር በመስጠት ላይ እንገኛለን አቶ መንግስቱ ጭምዴሳ ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥ/አስኪያጅ

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በስሩ 15 ቅርንጫፎች ይገኛሉ፡፡ አምቦ፤ ነቀምት፤ በደሌ፤ ጊንጪ፤ ጊምቢ፤ ላሎ አሳቢ፤ባኮ ቅርንጫፎች እና 8 ሌሎች ተጨማሪ ቅርንጫፎች በማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ሥር የሚገኙ ናቸው፡፡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ በስድስት ወር የስራ አፈጻጸም በሁሉም የመመዘኛ መስፈርቶች ተገምግሞ የ3ኛ ደረጃ በማግኘት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ ለዚህ ደረጃ መብቃቱ ትልቅ ስኬት ነው ያለው የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ጭምዴሳ ሆኖም ግን ካለው የአካባቢ ጸጥታ አንጻር በብድር ማስመለስ አሁን ላይ በጣም እንደተቸገሩ ገልጸዋል፡፡ ከባንክ አገልግሎት በርቀት ላይ ለሚገኙ የገጠር ማኅበረሰብ ክፍሎችን በቁጠባና ብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ከ24 አመት በላይ ሲያገለግል የቆየ በመሆኑ በደንበኞች ዘንድ ተመራጭና አስተማማኝ ተቋም አድርጎታል፡፡ ተቋሙ በአገልግሎት ጥራቱና ተደራሽነቱ የቀጠለ ቢሆንም በወቅታዊ የአካባቢ ፀጥታ ምክንያት በገጠር ለሚገኙ ደንበኞች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም ብድር ለማስመለስ መቸገራቸውን አቶ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡ ይህን ችግር ታሳቢ በማድረግ በተጠና መንገድ ትላልቅ ብድሮችና ከተማ ተኮር የሆኑ የፋይናንስ አቅርቦቶችን በማመቻቸት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ብለዋል የሰሜን ምዕራብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ፡፡ የ2014 ዓ.ም የ6 ወር የቅርንጫፎች የሥራ አፈጻጸም በመገምገም ከ1 እስከ 3 ደረጃ ለወጡት የማበረታቻ ሽልማት ስለመሰጠቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

Leave a Reply