You are currently viewing <strong>ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ 510 ልጆች የገና ሥጦታ ተበረከተ</strong>

ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ 510 ልጆች የገና ሥጦታ ተበረከተ

ታህሳስ 25/2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ በዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አስተባባሪነት ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ልጆች በተዘጋጀ የገና ሥጦታ መረሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ለ510 ልጆች የአልባሳት ስጦታ አበርክቷል፡፡

ተቋሙን በመወከል ስጦታውን ያበረከቱት የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳ ሲሆኑ ተቋሙ ልጆች የተሻለ ህይወት ነገን እንዲኖሩ ለማስቻል ትኩረት አድርጎ መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ዋና ሥራ አስፈጻሚው  ይህንን የልጆች ተጋላጭነትና ጉዳት በተወሰነ መልኩ የሚቀርፍ ሀሳብ ላመነጩና  ላስተባበሩ አካላት የላቀ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ ተቋማችን ተመሳሳይ መረሀ ግብሮችን በቁርጠኝነት እንደሚያግዝና እንደሚሳተፍ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የአስተባባሪዉ አካል ተወካይ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናት ስጦታ ላበረከቱ የምስጋና ወረቀት  በመስጠት ለልጆች የተበረከተው የገና ሥጦታ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚኖሩ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ልጆች ይውላል ብለዋል፡፡

Leave a Reply