You are currently viewing ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ

ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ

በማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ደረጃ አስጠብቀን እንሄዳለን አቶ ይድነቃቸው አምሳል የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ደቡብ አካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥ/አስኪያጅ

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ደቡብ አካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በስሩ 12 ቅርንጫፎች ሲገኙ ተቋሙ የያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ከማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስር 135 ሠራተኞች በቋሚነት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
እንደ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ28ሺህ በላይ ተበዳሪ ደንበኞችና ከ67ሺህ በላይ ደግሞ የቁጠባ ደንበኞች ይገኛሉ ያሉት አቶ ይድነቃቸው በውስን የሰው ሀይል ጥራት ያለው አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል፡፡ የቁጠባ መጠን ማሳደግና የብድር አመላለስ ጥራት መጠበቅ ላይ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ተገልጿል፡፡
በቁጠባና ብድር ስርጭት በአካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፎች ሥራቸውን ከተቀመጠው እቅድ አንጻር ተፈጻሚ እንዲያደርጉ የማስተካከያ እርምጃዎችን እየወሰደን እንገኛለን ብለዋል የደቡብ አካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፡፡
አክለውም ሁሉም ቅርንጫፎች የአገልግሎት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉና ወደ ተሻለ ቁመና እንዲደርሱ ውጤታማ የቁጠባና ብድር አገልግሎት በከተማና በገጠር ለሚኖሩ ኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲሰጡ የአመለካከት ለውጥ በሁሉም ቅርንጫፎች እንዲመጣ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ደንበኞች ለተቋሙ ያላቸው መልካም እይታና የአገልግሎት እርካታ ከምንሰጠው የአገልግሎት ጥራትና ደረጃ የተነሳ በመሆኑ ሰራተኞቻችን የደንበኞችን መረጃ በጥንቃቄ ይይዛሉ ሁልጊዜ ለማገልገል ተነሳሽነት አላቸው በማለት ተናግረዋል አቶ ይድነቃቸው አምሳል፡፡

Leave a Reply