You are currently viewing ሁሉም ቅርንጫፎች በኮር ባንኪንግ ሲስተም መገናኘታቸው ለዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መሰረት ነው

ሁሉም ቅርንጫፎች በኮር ባንኪንግ ሲስተም መገናኘታቸው ለዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መሰረት ነው

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የቅርንጫፍ ብዛት 97 ደርሷል፡፡ ተቋሙ በአመቱ 100 ቅርንጫፍ የመድረስ እቅድ ይዞ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ቅርንጫፍ መክፈት ጎን ለጎን ሁሉም ቅርንጫፎች ዘመኑ የደረሰበትን ዘመናዊ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲኖራቸው ያለሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ቅርንጫፎቹ በሙሉ ቀልጣፋና ፈጣን ብሎም ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት ለደንበኞች እንዲሰጡ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለሰራተኞች በመስጠት የልቀት ተቋም የመሆን ግብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ የኮርባንኪንግ ሲስተም በሁሉም ቅርንጫፎች ተግባራዊ እንዲሆን በ32 የስልጠና ዙር ከ135 ሠራተኞች በላይ አሰልጥኗል፡፡ አቶ አብረሃም አባይነህ የአይ ሲቲ መምሪያ ዋና ኃላፊ የኮርባንኪንግ ሲስተም በሁሉም ቅርንጫፎች ተግባራዊ መሆን ስኬት አስመልክተው ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የሰው ሀይል ምደባ፤ የመናጅመንትና ቦርድ ቁርጠኝነት፤ ለፕሮጀክቱ ትግበራ የተዋቀረ ቴክኒካል ቲም ትጋት እና የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅት መልካም ትብብር ነው ብለዋል፡፡

የኮርባንኪንግ ሲስተም ተግባራዊ መሆን ተቋሙ በቀጣይ የዲጅታል ባንኪንግ ሲስተም ለመጀመር የሚያስችለውን መደላድል ይፈጥራል ብለዋል ዋና ኃላፊው፡፡ አክለውም የተቋሙና የደንበኞችን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ እንደ መምሪያ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በተዘረጋው የመሰረተ ልማት ልክ ከባንክ አገልግሎት በርቀት ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚና ተደራሽ የሚያደርጉ ቀላልና ምቹ የሆኑ ዘመናዊ አገልግሎቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል ብለዋል አቶ አብረሃም አበይነህ፡፡

Leave a Reply